መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

መንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ርዕሰ አድባራት መንበረ ፀሐይ እንጦጦ ማርያም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ምስካየ ኅዙናን መድኃኔኃለም ገዳም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ደብረ ጽጌ ቅድስ ኡራኤል

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

መንበረ መንግሥት ቅ/ገብርኤል ገዳም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ደብረ ኃይል ራጉኤል

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/590538kidste_mariam.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/895720giorgis.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/903816bole_medhaniealem.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/683566trinity.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/821897entoto_mariam.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/310283meskaye_1.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/904160BEATA_MARIAM.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/578084urael.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/812647gebrie_gedam.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/681179raguel.jpg
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለገዳማትና አድባራት የዕለት ገንዘብ ስብሳቢና ገንዘብ ያዥ በገንዘብ አያያዝ ላይ ሥልጠና መስጠት ጀመረ

0084

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በርእሰ ከተማው በሚገኙ ገዳማትና አድባራት ለተመደቡ ዋና ገንዘብ ያዥና የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢዎች በገንዘብ ገቢና ወጭ አያያዝና አመዘገብ ዙሪያ ለ15 ቀናት ያህል የሚቆይ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና እየተሰጣቸው ሲሆን የስልጠናው ሂደትም በቃል/ በቲኦሪና /በተግባር (በኮምፒውተር በታገዘ) እንደዚሁም በቡድን እየተመደቡ የጋራ ውይይት በማድረግና ከዚያም አስፈላጊውን ጥያቄ በመጠየቅና ሐሳብም በመስጠት ስልጠናውን በተሳካ ሁኔታ እየተከታተሉት ይገኛሉ፡፡
የሰልጣኞች ቁጥር ብዛትም 340 ይደርሳሉ፤ ሰልጣኞቹ ከሰባቱም ክፍላተ ከተሞች የተውጣጡ ሲሆን ከአንድ ገዳም ወይም ደብር ሁለት ሰልጣኞች ተመድበዋል፤ በሰባቱ ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነትም የተመደቡ ገንዘብ ያዦች የስልጠናው ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡ ሊቀ ተጉኃን ገብረ መስቀል ድራር የሀገረ ስብከቱ የቁጥጥር ዋና ኃላፊ የስልጠናውን ሂደት አስመልክተው  በሰጡት ማብራሪያ ሰልጣኞቹ ከዘመኑ የሒሳብ አሠራር ጋር በማነፃፀር የሒሳቡን አሠራር እንዴት አድርገው ማሳለፍና መመዝገብ እና ሪፖርት ማድረግ እንዳለባቸው በተመለከተ የቲኦሪና የተግባር ሥልጠና እንዲወስዱ ለማድረግ ሥልጠናው ግንቦት 9 ቀን 2009 ዓ.ም ተጀምሮ በተገቢው ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ሥልጠናውን የሚሰጡት ሙያተኞች ሀገረ ስበከቱ ለዚሁ ለሥልጠና ሥራ ባስቀመጠው የሒሳብ ባለሙያና በተቋም ደረጃ በሚጋበዝ ባለሙያ ነው፡፡ ቀደም ሲል በሁለትና በሦስት ዙር የገዳማቱና የአድባራቱ የሒሳብና የቁጥጥር ሠራተኞች ስልጠና እንዲሰጣቸው ተደርጎ በተገቢና በተሳካ ሁኔታ ስልጠናው ተካሂዷል፡፡ በተሰጠውም ሥልጠና መሠረት ወደ ሥራ የተገባበት ሁኔታ አለ፡፡
ለዚሁም አጋዥ እንዲሆን ለሁሉም ገዳማትና አድባራት የፋይናንስ አሠራርንና አመዘጋገብን በሚመለከት ሥልጠናው ተሰጥቷል፡፡ የኦዲትና ቁጥጥር ማንዋልም ለሁሉም ገዳማትና አድባራት ተሠራጭቷል፡፡
የንብረትና የገንዘብ ሞዴላ ሞዴሎችን ከዘመናዊ የሒሳብ አሠራር ጋር እንዲጣጣሙ ተደርጎ በአዲስ መልክ አንጋፋ በሆነው የቤተ ክርስቲያናችን ማተሚያ ቤት ትንሣኤ ዘጉባኤ አሳትመን ለሁሉም ገዳማትና አድባራት እያሰራጨን እንገኛለን፡፡ ይህም በ2009 ዓ.ም የበጀት ዓመት በከፊል ወደትግበራ እየገባን ነው ያለነው፡፡
እንደ ሀገረ ስብከታችን እቅድና ፕሮግራም ከ2010 ዓ.ም የበጀት ዓመት ጀምሮ በሁሉም ገዳማትና አድባራት ዘመናዊ የሒሳብ አሠራር ይገባል ብለን እቅድ ይዘናል፡፡
ሥልጠናውም በተከታታይና በተፋጠነ መልኩ የሚሰጠው የሒሳብ፣ የቁጥጥርና የገንዘብ ያዥ  ሠራተኞች ለእቅዱ ተፈጻሚነት ቀዳሚ ስለሆኑ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የሁሉም አስተማሪና መካሪ፣ በዘመናዊ አሠራርም ቀዳማዊት እንደመሆንዋ መጠን አሁንም እንደ ጥንታዊነቷና እንደ ታሪካዊነቷ ታሪኳ ተጠብቆ ሥራዎችን ለመሥራት፣ የለውጥ አገልጋዩም ሆነ ተገልጋዩም ባንድነት በመሰለፍ  ለውጡን ባጭር ጊዜ ለማየት  እንድንችል ሁሉም የእኔ ነው፣ ይመለከተኛል በማለት ሥራው በዘመናዊ እና በሠለጠነ መልኩ እንዲከናወን ማድረግ ይገባል፡፡
አቶ ገብረ ሕይወት አስገዶም የሀገረ ስብከቱ የሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ኃላፊ በበኩላቸው በሰጡት ማብራሪያ በዋናነት የሥልጠናው ተጠቃሚ መሆን የሚገባቸው የእለት ገንዘብ ሰብሳቢዎችና ገንዘብ ያዦች ናቸው፡፡  ምክንያቱም በመጀመሪያ ከምዕመናን ጋር ግንኙነት ያላቸው እና ንብረትም ሆነ ገንዘብ የሚሰበስቡ እነርሱ ናቸው፡፡
ይሁን እንጂ ቀደም ብሎ በሀገረ ስብከቱ በተያዘው መርሐ ግብር መሠረት የገዳማቱ የሒሳብ እና የቁጥጥር ሠራተኞች ስለሰለጠኑ በዚያው ለመቀጠል ታስቦ እንጂ በመጀመሪያ መሰልጠን የሚገባቸው የእለት ገንዘብ ሰብሳቢዎችና ገንዘብ ያዦች ነበሩ፡፡
ስለዚህ የእለት ገንዘብ ሰብሳቢዎችና ገንዘብ ያዦች ሥልጠና መውሰዳቸው ተገቢ በመሆኑ ነው አሁን መርሐግብሩ እየተካሄደ ያለው፡፡ ከዚህ በፊት በነበረው የገንዘብ አሰባሰብና አያያዝ ሁኔታ ችግሮች አልተከሠቱም፡፡ ነገር ግን ዓለምን የዋጀውን የሒሳብ አሠራር ግልፅነት እና ተጠያቂነት እንዲኖረው ሒሳቡን ለማዘመን ካልሆነ በስተቀር ቀደም ሲል የነበረው የሒሳብ አሠራርና የገንዘብ አሰባሰብ አባቶቻችን ያቆዩልን አሠራር ከዘመኑ ጋር የሚሄድ ባለመሆኑ እንጂ የሥራ ችግር ኖሮበት አይደለም ወደዚህ አሠራር የመጣነው፡፡ በ2008 ዓ.ም የበጀት ዓመት ሥልጠና ተካሂዷል፡፡ 2009 ዓ.ም የበጀት ዓመትም ከሠላሳ በላይ የገዳማትና አድባራት የሒሳብ ሠራተኞች ወደዘመናዊው ሥራ ገብተው እየሠሩ ይገኛሉ፡፡
ኦዲቱም የሚካሄደው በዘመናዊው የሒሳብ አሠራር መሠረት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በተሰጠው ስልጠና መቶ በመቶ ለውጡ መጥቷል ባይባልም በተወሰነ ሂደት ለውጡ መጥቷል ብለን እናስባለን፡፡ ምንክንያቱም ለውጡ ሲመጣ ቀናትንና ወራትን እያስቆጠረ የሚመጣ ስለሆነ ለውጡ 50% ታይቷል (ደርሰናል)፡፡ ሥለጠናው ለወደፊቱም ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ከዚህ በፊት የሰለጠኑትም ቢሆን የበለጠ ግንዛቤያቸውን ለማስፋት እንዲችሉ ስልጠናው ቀጣይነት እንዲነኖረው ነው እቅድ የተያዘው፡፡ በሒሳብ ክፍል፣ በዕለት ገንዘብ ሰብሳቢ፣ በገንዘብ ያዥና በንብረት ክፍል ያለው አሠራር አጠቃላይ ግልፅነት እንዲኖረው ሥልጠናው በ2010 የበጀት ዓመትም ይቀጥላል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ጥንታዊትና ቀዳማዊት እንደመሆንዋ መጠን አስተማሪ የነበረች ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡
ስለዚህ በአስተማሪነት ሥራዋ እንድትቀጥል ያለውን የዘመናዊውን አሠራር በበለጠ አጠናክራ እንድትቀጥል ለማድረግ ሁሉም ወደዚህ መስመር እንዲገባ ነው የሚአስፈልገው፡፡ለዚህ ለውጥ ሁሉም ያገባኛል፣ ይመለከተኛል ብሎ ለለውጡ እንቅስቃሴ ተባባሪ ሊሆን ይገባዋል ብለዋል፡፡
በተያያዘ ዜና በ2009 የበጀት ዓመት ለኦዲቲንግ ሥራ የሚሠማሩ የሀገረ ስብከቱና ለክፍለ  ከተማ ሠራተኞች ከግንቦት 14/2009 እስከ ግንቦት 23/2990 ዓም ድረስ የሚቆይ የኦዲቲንግ ሥልጠና በመሠጠት ላይ ነው፡፡

 
የገብረ ሰላም በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከበረ!!!

0035

በየዓመቱ በትንሣኤ ዋዜማ ሲከበር የቆየው የገብረ ሰላመ በዓል በዘንድሮው ዓመት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፖትርያርክ ርእሰ ሊቃ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም፣ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር ጎይቶኦም ያይኑ እና የሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ገዳማት እና አድባራት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በተገኙበት ዛሬ ቅዳሜ ሚያዝያ 7 ቀን 2009 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡  በተረኛው ደብር በደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ደብር ካህናት ጸሎተ ወንጌል ተደርሷል፡፡
“አሜሃ መልአ ፍስሐ ዓፉነ፤ ወተኀሥየ ልሳንነ፤ አሜሃ ይቤሉ አሕዛብ፡፡” በዚያን ጊዜ አፋችን ደስታን ሞላ፤ አንደበታችንም ሐሴትን ሞላ፤ በዚያን ጊዜ በአሕዛብ ዘንድ፡፡ መዝ. 125÷2 የሚለው የዳዊት መዝሙር በዲያቆዩ በዜማ ተዚሟል፡፡
ከዚያም በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 19 ላይ የተጻፈው የወንጌል ቃል በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በንባብ ተሰምቷል፤ በወንጌሉ እንደተጻፈው ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተሰቀለበት ወቅት እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም እና ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በመስቀሉ ሥር ቆመው እንደበርና ኢየሱስ ክርስቶስም ከኀዘናቸው እንዳጽናናቸው ያብራራል፡፡
በመቀጠልም ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ ለዘተንሥአ እሙታን ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚል ያሬዳዊ መዝሙር በተረኛው በደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ደብር ሊቃውንት ቀርቧል፤ ከዚያም አንሰ እረክብ ሰላመ በእንቲአሁ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ወልድ እሁየ ሊተ ወአነ ሎቱ አፈቅሮ እስከ አመ ፈቀደ የሚል ያሬዳዊ ወረብ በቅዱስ ዑራኤል ደብር ወጣቶች ቀርቧል፡፡ ከዚያም በማያያዝ ሁለት የቅኔ ሊቃውንት በዓሉን የተመለከተ ቅኔያት አቅርበዋል፡፡
በመቀጠልም በብፁዕ አቡነ እንድርያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሊቃውንት ጉባኤ የበላይ ኃላፊ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል፡፡ ብፁዕነታቸው በሰጡት ትምህርት በኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ስደት እና ባርነት ተወግዷል፤ በነፍስ በሥጋ ተቆራኝተው የነበሩ አጋንንት ተበትነዋል፤ የ5500 ዓመት መከራ አልቋል፤ ምድርና ሰማያት ተቀድሰዋል፤ በፈጣሪ ደም ዓለም ተቀድሷል፤ ለሰው ልጆች ካሳ ተፈጽሟል፤ ልጅነት ተሰጥቷል፤ ይህች ዕለት በእግዚአብሔር ዘንድ የድኅነት እቅድ ተይዞባት የነበረች እለት ናት፤ ስብከተ ወንጌል በአራቱም ማዕዘን ተሰራጭቷል፤ መርገመ ሥጋ እና መርገመ ነፍስ ጠፍቷል፤ ይሁዳ ዘነፍስ በዓልህን አድርግ ተብሏል፤ የማናይ ታምራት አይቶ ስላመነ ከአባቱ ከአዳም ቀድሞ ገነት ገብቷል፤ በጨካኙ ጠላት ተይዘው የነበሩት ነፃነት ተሰብኮላቸዋል በማለት ብፁዕነታቸው ሰፋ ያለ ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ ፖትርያርኩ ባስተላለፉት አባታዊ ትምህርት እና ቃለ ምዕዳን ዛሬ በዚህ ካቴድራል የተገኘነው የገብረ ሰላመን በዓል ለማክበር ነው፤ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙስና መቃብርን ያሸነፈበት በዓል ስለሆነ በዓሉ የሰላም በዓል ነው፤ የሰው ልጆች ከዘለዓለማዊ የሲዖል እሥራት የተፈቱበት በዓል ስለሆነ በዓሉ ትልቅ በዓል ነውና እንኳን ለዚህ ትልቅ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! በማለት አባታዊ ቡራኬ እና ቃለ ምዕዳን ካስተላለፉ በኋላ የሰላምና የነፃነት ምልክት የሆነውን ቄጤማ ከብፁዓን ሊቃ ጳጳሳት ጀምሮ በካቴድራሉ ለተገኙት ሊቃውንት እና ምእመናን በመስጠት የበዓሉን ምሥራች አብሥረዋል፡፡

 
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የ2009 ዓ.ም የትንሣኤ በዓልን አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ

pp009

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱምወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በእንተ በዓለ ትንሣኤ ቅድስት ዘእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሎቱ ስብሐት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
• በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤
• ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ
• የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
• በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ
• እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤
በትንሣኤው ኃይል በመቃብር ውስጥ በስብሶ መቅረትን ሽሮ ትንሣኤ ሙታንን ያበሠረ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዘጠኝ ዓመተ ምሕረት በዓለ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!!
“ወሰበረ ኆኃተ ብርት፤ ወቀጥቀጠ መናሥግተ ዘሐጺን፤
የናስ ደጆችን ሰባበረ ፣ የብረት መወርወሪያዎችንም ቀጥቅጦ ቈራረጠ፤(መዝ 107፡16)፡፡
ይህ አምላካዊ ኃይለ ቃል ወልደ እግዚአብሔር የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ በመሥዋዕትነቱ ብቃት እንደ ናስ የጠነከሩትን የኃጢአት ደጆች እንደሚሰባብር፣ እንደ ብረት የጸኑትን የሞት ብረቶች ቀጥቅጦ በመቆራረጥ እንደሚያስወግድ መንፈስ ቅዱስ በዳዊት አንደበት የተናገረው ቃለ ብሥራት ነው፤
የኃይለ ቃሉ ምሥጢራዊ ይዘት በጠንካራ ነገር የተዘጉና በጽኑ መወርወሪያዎች ክርችም ብለው የተዘጉ ደጆች መኖራቸውን ጠቁሞ፣ እነዚህን ሰባብሮና ቀጥቅጦ በሩን የሚከፍት አንድኃያል መሢሕ እንደሚመጣ የሚያመለክት ነው፡፡
በመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንደምናነበው የሰው መኖሪያ የነበረው ነገተ ኤዶም በኃጢአተ ሰብእ ምክንያት በፍትሐ እግዚአብሔር ሲዘጋ፣ በሰይፈ ነበልባል እንደተከረቸመ፣ ኪሩባውያን ኃይላትም በጥበቃ እንደተመደቡበት በግልጽ ተመዝግቦአል፡፡
ይህ የጽድቅ የክብርና የሕይወት ደጅ በዚህ ሁኔታ ሲዘጋ፣ ለሰው ልጅ የቀረለት መኖሪያ ለሰይጣንና ለሠራዊቱ የተዘጋጀው፣ እሳቱ የማይጠፋ፣ ትሉ የማያንቀላፋ የእቶነ እሳት ከተማ ነበረ፤
ለመለኮታዊ ሱታፌና ለዘላለማዊ ሕይወት ታድሎ የነበረው የሰው ልጅ ለእግዚአብሔር ባለመታዘዙ ምክንያት ለአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዓመታት ያህል የተጋዘው ከላይ በተጠቀሰው የዲያብሎስ ከተማ ነበር፡፡
የዚህ ከተማ ደጆችና በሮች፣ መዝጊያዎችና መወርወሪያዎች ኃጢአት፣ ፍትሐ ኵነኔና ሞተ ነፍስ ወሥጋ ነበሩ፤ የሰው ልጅ ኃጢአትን ስለ ሠራ እግዚአብሔር የቅጣት ፍርድን ፈረደበት፤ ቅጣቱም የነፍስና የሥጋ ሞት ነበረ፤ እነዚህ ነገሮች እርስ በርስ እንደ ሰንሰለት ተያይዘው የዲያብሎስን ከተማ የናስና የብረት ያህል ጠንካራ ደጅ እንዲሆን አድርገውታል፡፡
ይህንን በር ሰብሮና ፈልቅቆ የሰዎችን ነፍሳት ከዲያብሎስ ከተማ መዞ ማውጣት ለፍጡር ፈጽሞ የማይቻል ነበረ፤ ሦስቱም ነገሮች ከፍጡራን ዓቅም በላይ በመሆናቸው አምላካዊ ኃይል የግድ አስፈላጊ ሆነ፡፡
በዚህም ምክንያት ጌታችን ሥጋችንን ተዋሕዶ በዚህ ዓለም በመገለጥ እኛ ከኃጢአት ከፍትሐ ኵነኔና ከሞተ ነፍስ የምንድንበት መንገድ እርሱ ብቻ መሆኑን በአጽንዖት አስተማረ፡፡
በመጨረሻም እንደ ትምህርቱና እንደ ቃሉ በመስቀሉ ኃይል ወይም በመሥዋዕትነቱ ብቃት ሦስቱ ነገሮች ማለትም ኃጢአት፣ ፍትሐ ኵነኔና ሞተ ነፍስ ከሰው ጫንቃ ላይ እንዲወገዱ አደረገ፤
ለሰው የማይቻል የነበረ ይህ ግብረ አድኅኖ በተዋሕዶ አምላክም ሰውም ለሆነ ለጌታችን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የሚቻል ነበረና በእርሱ መሥዋዕትነት እውን ሆነ፡፡
ጥንቱም ለሰው ልጅ ሕይወትና ክብር ጠንቆች የነበሩ እነዚህ ሦስቱ ነበሩና እነሱ ተሰባብረውና ተቀጥቅጠው ሲወገዱ በሲኦል ይኖሩ የነበሩ የሰዎች ነፍሳት በአጠቃላይ ዓለም ከመፈጠሩ በፈት ወደተዘጋጀላቸው ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር ተመልሰው ገቡ፡፡
 ከክርስቶስ ሞት በኋላ የነፍሳተ ሰብእ ጉዞ ወደ ዲያብሎሰ ከተማ ወደ ሲኦል መሆኑ ቀርቶ ወደ እግዚአብሔር ከተማ ወደ ጽዮን መንግሥተ ሰማያት ሆነ
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት
እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች በዓለ ትንሣኤን ከምንም በላይ በላቀ ሁኔታ የምናከብርበት ምክንያት ኃጢአት ፍትሐ ኵኔና ሞተ ነፍስ ወዲያ ተሽቀንጥረው በምትካቸው በክርስቶስ ቤዛነት ጽድቅን ይቅርታንና ሕይወተ ነፍስን የተቀዳጀንበትና ከድል ሁሉ የበለጠ የድል ቀን በመሆኑ ነው፡፡
ሁላችንም መገንዘብ ያለብን ዓቢይ ነገር የክርስቶስ ድርጊቶች በሙሉ ለሰው ድኅነት ሲባል ብቻ የተደረጉ እንጂ ለእግዚአብሔር የሚፈይዱት አንዳች ምክንያት የሌላቸው መሆኑን ነው፤ ይህም ማለት በክርስቶስ የተፈጸሙ ድርጊቶች በሙሉ ለእኛ ሲባል የተደረጉ መሆናቸውን መገንዘብ አለብን ማለት ነው፡፡
ክርስቶስ ተሰቀለ ሞተ ተቀበረ ተነሣ ሲባል እኛ ተሰቀልን ሞትን ተቀበርን ተነሣን ማለት እንደ ሆነ ልብ ብለን ልናስተውል ይገባል፤እኛ ተሰቅለን ሞተንና ተቀብረን የኃጢአታችንን ዕዳ የመክፈል ዓቅም ስላጣን ለኛ ያልተቻለውን ጌታችን ስለ እኛ ብሎ፣ በእኛ ምትክ ሆኖ ለኃጢአታቸን መከፈል የነበረበትን ዋጋ ሁሉ ከፍሎ አድኖናልና ነው፡፡
እኛ በክርስቶስ ቤዛነት ነጻነታችንን ተቀዳጅተን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ዳግመኛ መግባት የቻልነው ክርስቶስ የከፈለው መሥዋዕትነት ለእኛ ተብሎ ስለ እኛ የተደረገ በመሆኑ ነው፡፡
የክርስቶስ ትንሣኤ የእርሱ ትንሣኤ ብቻ እንደሆነ አድርገን የምንገነዘብ ከሆነ ታላቅ ስሕተትም ኃጢአትም ነው፤ ኃጢአት ኵነኔና ሞተ ነፍስ የሌለበት እርሱማ ምን ትንሣኤ ያስፈልገዋል! ትንሣኤ ለሚያስፈልገን ለእኛ ተነሣልን እንጂ፤
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን አስመልክቶ ሲያስተምር “እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጸጋ ስለሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ አስነሣን ከእርሱ ጋርም በሰማያዊ ስፍራ አስቀመጠን” ብሎአል፤ (ኤፌ 2፡4-7)፡፡
ከዚህ አኳያ የቀን ጉዳይ ካልሆነ በቀር የትንሣኤያችን ጉዳይ በክርስቶስ ትንሣኤ የተረጋገጠና ያለቀለት ነገር እንደሆነ ማስተዋል፣ መገንዘብ፣ መረዳትና፣ ማመን ይገባናል፡፡
የጌታችን ትንሣኤ ለሰው ልጅ ተብሎ የተደረገ በመሆኑ የእኛ ትንሣኤ ነው ብለን ሁሌም መውሰድና መቀበል አለብን፤ ምክንያቱም የክርስቶስ ትንሣኤ የመጨረሻ ግቡ የሰው ልጆች ትንሣኤን ማረጋገጥ ነውና፤
 የትንሣኤ ዕድል በክርስቶስ ቤዛነት ለሁሉም ተሰጥቶአል፤ አዋጁም ሕጉም በክርስቶስ ትንሣኤ ጸድቆአል፤ የቀረ ነገር ቢኖር የመጨረሻው ተግባራዊ ፍጻሜ ነው፤ እርሱም ቀነ ቀጠሮ የተያዘለት ስለሆነ ወደዚያው በእምነትና በሥነ ምግባር መገስገስ ነው፤ ሰውን ለዚህ ዓቢይ ጸጋና ዕድል ያበቃ እግዚአብሔር አምላካችን ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት፤
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሠራውና ያስተማረው ሁሉ ምን ለማግኘት ነበረ ተብሎ ቢጠየቅ በአጭር ዐረፍተ ነገር “ሰውን ለማዳን” ነዋ ! ብሎ መመለስ ይቻላል፤ እውነቱም ሐቁም ይህና ይህ ብቻ ነው፤
ይህን ያህል ውጣ ውረድና ይህን ያህል ዋጋ ያስከፈለ የሰው መዳን በእግዚአብሔር ዘንድ ምን ያህል ተፈላጊ እንደሆነ በአድናቆት መመልከትና መቀበል  ታላቅ አስተዋይነት ነው፡፡
በዚህ ሰውን የማዳን የእግዚአብሔር ክንውን እኛ ሰዎች የእግዚአብሔር ልጆች ለመሆን በቅተናል፤ ልጆቹም ሆነናል፤ ታድያ ልጅ በጠባይም፣ በመልክም በሥራም አባቱን ቢመስል ጌጥም የክብር ክብርም ነውና በሁሉም ነገር አባታችንን መከተልና መምሰል ከእኛ ይጠበቃል፡፡
እግዚአብሔር አባታችን እንደመሆኑ፣ እኛም ልጆቹ እንደመሆናችን መጠን የአባታችንን ተቀዳሚ መደበኛና ቀዋሚ ሥራ የሆነውን ሰውን የማዳን ሥራ ሳናቋርጥ የማስቀጠል ግዴታ አለብን፡፡
ዛሬም ዓለማችን የሚያድናት፣ እስከ ሞት ድረስም ደርሶ ቤዛ የሚሆናት፣ ሰላምንና ነጻነትን የሚያቀዳጃት የእግዚአብሔር ልጅ ትፈልጋለች፡፡
የጌታችን ትንሣኤ ከመቃብር በመነሣትና ሙታንን በማስነሣት ብቻ የሚገለጽ አይደለም፤ ጌታችን ከመሞቱና ከመነሣቱ በፊት ብዙ ሰዎችን ከረኃብ፣ ከበሽታ፣ ከሥነ-ልቡና ውድቀት አስነሥቶአል፤ ከተሳሳተ አመለካከት፣ ከጭካኔ፣ ከመለያየት አባዜም በተአምራትም በትምህርትም አድኖአል፡፡
ጌታችን ሰውን የማዳን ሥራ በእርሱ ብቻ ተሠርቶ እንዲቀር አላደረገም፤ እኛም እንድንሠራውና እንድንፈጽመው አዘዘ እንጂ፡፡
ከዚህ አንጻር በክርስቶስ ዘመን እንደነበረው ሁሉ ዛሬም ብዙ በሽተኞች የሚያድናቸው አጥተው በየጎዳናው፣ በየሰፈሩ፣ በየመንገዱ፣ ወድቀው ይሰቃያሉ፤ እነዚህን ማን ያድናቸው?
የተመጣጠነና በቂ ምግብ አጥተው ብዙ ሕጻናት፣ እናቶችና አረጋውያን በረኃብ አለንጋ ይገረፋሉ፤ ኅብስቱን አበርክቶ እነርሱን ማን ይመግባቸው?
በተሳሳተ አመለካከት ለሥነ ልቡና ውድቀት፣ ለቀቢፀ ተስፋና እንደዚሁም ለስሑት ትምህርተ ሃይማኖት ተጋልጠው ሃይማኖታቸውንና ታሪካቸውን በመጻረር የሚገኙ ብዙ ናቸው፤ እነዚህን ማን አስተምሮ ወደ እውነቱ ይመልሳቸው?
በእግዚአብሔር ዘንድ እነዚህን ሥራዎች መሥራትና ማስተካከል የሕዝበ ክርስቲያኑና የመምህራነ ወንጌል ግዴታዎች ናቸው፡፡
በማኅበረ ሰቡ ሥር ሰደውና ተስፋፍተው የሚታዩት እነዚህ መሰል ሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ችግሮችን በወሳኝነት ለመቋቋም ትምህርትና ልማት መተኪያ የሌለው ሚና ይጫወታሉ፤
ለሀገራችን ድህነት መወገድ ቁልፍ መፍትሔ ሃይማኖትና ልማትን አጣምሮ መያዝና በእነርሱ ጸንቶ መኖር አማራጭ የሌለው ነው፡፡
ከነዚህ ውጭ የሆነ ኑሮ ምንም ቢሆን ምሉእ አይደለም፤ ጣዕምም የለውም፤ የሰውን ሁለንተናዊ ሕይወት ለማዳንሁለቱንም በተግባር መተርጐም ያስፈል ጋል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ በእነዚህ ነገሮች የታደለች እንደነበረችና እነዚህን አጣምራ በመያዝ የት ደርሳ እንደነበረ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የሚታዩና የማይታዩ መረጃዎች ምስክርነታቸውን ከመስጠት ዛሬም  አልተገቱም፡፡
በአሁኑ ጊዜ ሀገራችን የተያያዘችውን የልማትና የሰላም ጉዞ አጠናክራ እስከ ቀጠለች ድረስ  ሕሙማን የሚፈወሱባት፣ ርኁባን ጠግበው የሚኖሩባት፣ በመንፈሳዊና በዘመናዊ ዕውቀት የበለፀጉ ዜጎች የሚታዩባት ሀገር የማትሆንበት ምክንያት ምንም የለም፡፡
መላው የሀገራችን ሕዝቦች በኑሮአቸወና በሕይወታቸው መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት የሚችሉት በሌላ ሳይሆን እነርሱ ራሳቸው እንደቀድሞ አባቶቻቸው በራስ በመተማመንና በልበ ሙሉነት፣ በትጋትና በቅንነት፣ በፍቅርና በስምምነት፣ በእኩልነትና በወንድማማችነት፣ በሰላምና በአንድነት በመቻቻልና በአብሮነት ሆነው በሚያስመዘግቡት የልማት ውጤት እንደሆነ መርሳት የለባቸውም፡፡
ሀገርን ለማልማትና የጠላትን ጥቃት በብቃት ለመመከት በአንድነት ሆኖ ከመታገል የተሻለ አማራጭ የለም፤ ስለዚህ ሕዝባችን እነዚህን እስከመቼውም ቢሆን በንቃት ሊከታተላቸውና ሊጠብቃቸው ይገባል፤ በአእምሮ የላቁ ሆኖ መገኘት በራሱ እውነተኛ ትንሣኤ ነውና፡፡
በመጨረሻም
የጌታችን ትንሣኤ “ሰውን የማዳን የእግዚአብሔር ዓላማን ያሳካ ፍጻሜ እንደሆነ ሁሉ የትንሣኤ ልጆች የሆን እኛ ሰውን ለማዳን በሚደረገው መንፈሳዊና ልማታዊ ርብርቦሽ ተሳትፎአችንን አጠናክረን እንድንቀጥል መንፈሳዊና አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፣፡፡
መልካም በዓለ ትንሣኤ ያድርግልን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ ይቀድስ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
 ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
 ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ሚያዚያ ፰ ቀን ፳፻ወ፱ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

 
<< ጀምር < ወደኋላ 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 ወደፊት > መጨረሻ >>

ገጽ 6 ከ 104

አድራሻ

አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ

ኢ-ሜይል: aadioces@gmail.com

ድረ ገጹ ውስጥ ይፈልጉ

ሀሳበ ባሕር(የዘመን ቁጥር)

ባሕረ ሐሳብ የዘመን መቁጠሪያ

ግጻዌ