መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

መንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ርዕሰ አድባራት መንበረ ፀሐይ እንጦጦ ማርያም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ምስካየ ኅዙናን መድኃኔኃለም ገዳም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ደብረ ጽጌ ቅድስ ኡራኤል

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

መንበረ መንግሥት ቅ/ገብርኤል ገዳም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ደብረ ኃይል ራጉኤል

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/590538kidste_mariam.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/895720giorgis.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/903816bole_medhaniealem.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/683566trinity.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/821897entoto_mariam.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/310283meskaye_1.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/904160BEATA_MARIAM.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/578084urael.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/812647gebrie_gedam.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/681179raguel.jpg
በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የዘመናችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተግዳሮቶችና የመፍትሔ ሃሳቦች በሚል ርእስ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀረበ

6139

በአዲስ አበባ ሀ/ስብከትና በሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ መምሪያ በተደረገ የጋራ ዝግጅት የዘመናችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተግዳሮቶችና  የመፍትሔ ሃሳቦች በሚል ርእስ የተጠና ጥናታዊ ጽሑፍ የሃገረ ስብከቱ ሥራ አስክያጅ መ/ር ጎይትኦም ያይኑ፤የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣የየአድባራቱ ሰባክያነ ወንጌል ሐላፊዎች፣ ሊቃነ መናብርትና የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ተወካዮች በተገኙበት በአዲስ አበባ ሃ/ስብከት አዳራሽ ታህሣሥ 14/2010 ዓ.ም ጥናታዊ ጽሑፉ ቀርቧል።ጥናቱ በሁለት ክፍል የቀረበ ሲሆን በተሳታፊዎች በኩል ለውይይት መድረኩ ክፍት ተደርጎ ነበር። በቀረበው ጥናት ላይ ቤተ ክርስቲያናችን በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ያጋጠሟት ተግዳሮቶችና ውጣውረዶች በርካታ ቢሆኑም የመልካም አስተዳደር እጦት፣ አግባባዊ የሆነ የአገልጋይነት ክብር አለመኖር፣ ለትክክለኛ ስራ ትክክለኛ ሰው አለመመደብና የመሳሰሉት መሆናቸው ተገልጾ ዋናውና ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ተግዳሮት ግን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አስተምህሮአዊ እንቅስቃሴና የእስላማዊ አክራሪነትና ጽንፈኝነት ናቸው ተብሏል።በጥናታዊ ዳሰሳው ላይ ቤተክርስቲያናችን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ የተበታተነ፣ ወጥነት የሌሌው፣ብዙ ትግል ጥቂት ውጤት በመሆኑ የችግሩ መስፋትና እልባት አለማግኘት ችግሩን እስካሁን ድረስ እንዲቀጥል አድርጎታል ከዚህም ጋር ተያይዞ ቤተክርስቲያናችን በርካታ ሊቃውንትና መምህራን እንዲሁም የስነ–መለኮት ምሩቃን ያሏት ባለብዙ አንጡራ ሃብት ያላት ብትሆንም የስብከተ ወንጌል መድረኳንና የሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሿን የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተምህሮ ጠንቅቀው በማያውቁ የመድረክ ሰዎች መወከሏ ሌላኛውና አንገብጋቢው ችግር መሆኑም ነው የተገለጸው። በየትኛውም መዋቅራዊ አደረጃጀት ባለው ተቋም ውስጥ የራሱ የሆነ ስልታዊ መዋቅር፣ኃላፊነትና ተጠያቂነት ያለው አካል፣የሚከናወኑ ክንውኖች፤ የሚሰሩ ስራዎችና በእቅድ የሚመራ የስራ ክንውን ቢኖራቸውም በየጊዜው አፈጻጸሙን የመገምገም፣ የመፈተሽና የማስተካከል እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የመለወጥም ስራ ጭምር ሲደረግ እንመለከታለን። በቤተክርስቲያናችንም ነገሩን በበላይነት የሚመራው አካል አትኩሮት በመስጠት የተደራጀና የሰለጠነ በቂ የሰው ሃይል በየዘርፉ በመመደብ፣ ያገባኛል የሚል የተቆርቃሪነት ስሜት በማስፈን፣ሐዋርያዊ አስተምህሮዋን በመጠበቅ፣ ቀኖናዋንና ሥርዓትዋን ዘመኑንና ትውልዱን በጠበቀ መልኩ በማሻሻልና በማስተካከል ሐዋርያዊ ግዴታዋን  ያለቸልታና ዝምታ   ልትወጣ ይገባታል። የችግሩ አሳሳቢነት በወፍ በረራ አስተምህሮ የሚቀረፍ ባለመሆኑ ቤተክርስቲያኒቱ ያሏትን ሊቃውንት አስተባብራና አጠንክራ መስራት እንዳለባትም በጥናቱ ለመዳሰስ ተሞክረዋል። ቤተክርስቲያኒቱ 10 ሚሊዮን አማንያንን በቀላሉ ለመዘረፍ ዋንኛ ምክንያት የእኛ አለመወያየት፣ አለመነጋገርና በጋራ አለመስራት መሆኑም  ተነስቷል።በታዳሚዎቹ ሰፋ ያለ ወይይት የተደረገ ሲሆን ብዙ አስተያየቶችም ተሰንዝሯል።
 በመጨረሻም የአዲስ አበባ ሃገረስብከት ሥራ አስኪያጅ መምህር ጎይትኦም ያይኑ  ከሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃና መምሪያ ሃላፊ መምህር እንቁ ባህሪ ንግግር በመቀጠል ባደረጉት የመደምደምያ ንግግር በቀረበው ጥናት ላይ አያይዘው የቀረበው ጥናት እንደ አንድ የቤክርስቲያን ችግር መሆኑን ቢያወሱም ሌሎች በርካታና አንገብጋቢ  የቤተ ክርስቲያን ችግሮች መኖራቸውንም ሳይናገሩ አላለፉም። ቤተክርስቲያናችን በቂ የሚባል የሰው ኃይል አላት፤ ነገር ግን ሁሉም አካላት ሐላፊነታቸውንና ድርሻቸውን በአግባቡ አልተወጡም።  ይህም የቀረበው ጥናት የት እንዳለንና ደረጃችንን በመጠኑ የሚያሳይ ቢሆንም ሌሎችንም ችግሮች አካትቶ የበለጠ ጥናት ልናደርግ ይገባናል በማለት ሐሳቡን አጠናክረዋል። ቤተክርስቲያኒቷ ከሲኖዶስ ጀምሮ እያንዳንዱ ቤት ድረስ የሚገባ መዋቅር  አላት። በጣም የሚሳዝነው ነገር ቢኖር በመዋቅሩ መሰረት አለመስራት፣ አግልጋዮች የተባበረና የተቀናጀ አንድነት አለመኖር፣ለአባቶች የሚገባውን ክብርንና የአባትነት ስሜት አለመስጠትና የመሳሰሉት ዘርፈ ብዙ ችግሮች መሆናቸውን አስርድተው ወደፊትም ሀገረስብከቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበርና የቅዱስነታቸውን መልካም ፍቃድ በመጠየቅ እንዲሁም  አባታዊ ምክራቸውን በማዳመጥ ለቤተ ክርስቲያን የሚበጀውንና የሚጠቅመውን ሁሉ ከማድረግ ችላ እንደማይል የውይይት መድረኮችም እንደሚቀጥሉ በመናገር ሐሳባቸውን ደምድመዋል።

 
“እውነተኛው የዓለም ብርሃን”

ብርሃን ሁሉን የሚያሳይና ለፍጡራን ሁሉ የሚጠቅም የተፈጥሮ ፀጋ ስለሆነ መልካሙ ነገር ሁሉ በብርሃን ይመሰላል፡፡ ይሁን እንጂ ከስነ ፍጥረት የሚገኝ ብርሃን ተቃራኒ ስላለው ጊዜያዊ እንጂ ዘላቂና አስተማማኝ አይደለም፡፡ ለምሳሌ፡ - ከፀሐይ፣ ከጨረቃና ከክዋክብት እንዲሁም ከእሳት ወይም ከኤሌክትሪክና ከመሳሰሉ የተፈጥሮ ውጤቶች የሚገኝ ብርሃን ጊዜያዊ እንጂ ቋሚና አስተማማኝ ስላልሆነ አንድ ጊዜ ይበራል ሌላ ጊዜ ደግሞ ይጠፋል፡፡ ምክንያቱም የፀሐይ ብርሃን በቀን በርቶ በሌሊት ጨለማ ይጋርደዋል፤ በቀንም ጥላ ይከልለዋል፡፡ ከጨረቃና ከክዋክበት የሚገኘውም ብርሃን በሌሊት እንጂ በቀን ደምቆ ሊታይ አይችልም፤ ሌሊትም ቢሆን ጊዜና ወቅት ይወስነዋል፡፡ ከእሳት የሚገኘው ደግሞ ተቀጣጣይ ነገሮች ሲታጡ ወይም በውኃ ኃይል እሳቱ ሲጠፋ ብርሃኑም አብሮት ይጠፋል፡፡ የኤሌክትሪኩም እንደዚሁ መስመሩ ሲቋረጥና አምፖሉ ሲቃጠል ብርሃኑም አብሮ ይቋረጣል፡፡ ስለሆነም በተፈጥሮ ሂደቶች የሚገኘው ብርሃን ሁሉ ተቃራኒ ስላለው እውነተኛ ብርሃን ሊባል አይችልም፡፡
ታዲያ እውነተኛ ብርሃን ማነው? መልሱን ከቅዱሳት መጻሕፍት ማግኘትና መረዳት እንችላለን፡፡ ሐዋርያውና ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በጻፈው የመረጀመሪያ መልእክቱ “መንዜንወክሙ ከመ እግዚአብሔር ብርሃን ውእቱ መጽልመትሰ አልቦ ኃቤሁ ወኢ አሐተኒ” (ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምንነግራችሁ መልእክት እግዚአብሔር ብርሃን ነው፣ ጨለማም በእሱ ዘንድ ፈጽሞ የለም፤ የምትል ናት) በማለት እውነተኛ ብርሃን እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ በግልጥ ጽፎአል (1ዮሐ. 1÷5)፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መምጣትና ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷም ነፍስን ነሥቶ ሰው ሆኖ የመወለዱ ምስጢር እንደ እንግዳ ደራሽ እንደውኃ ፈሳሽ በድንገት የሆነና የተፈጸመ ሳይሆን ገና ከመሆኑ አስቀድሞ በቅዱሳን ነቢያት ትንቢት የተነገረለትና ሱባዔ የተቆጠረለት ከመሆኑም በላይ በልዩ ልዩ ምሳሌዎች የተገለጠ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ከምሳሌዎቹም አንዱ ‹‹ብርሃን›› በመሆኑ ይህ ብርሃን የሚለው ስም ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የወጣለት ገና ሰው ከመሆኑ አስቀድሞ ከልደቱ በፊት በዘመነ ነቢያት እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በዚህም ምክንያት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትውፊትና ሥርዓት መሠረት ከበዓለ ልደቱ አስቀድሞ ያሉት ሦስት ሳምንታት የመጀመሪያው ስብከት ሦስተኛው ደግሞ ኖላዊ በመባል የሚከበሩ ሲሆኑ በስብከትና በኖላዊ መካከል ያለው ሳምነት ደግሞ ‹‹ብርሃን›› በመባል እንደሚከበር ይታወቃል፡፡ ‹‹ብርሃን›› ተብሎ በሚጠራው በዚሁ ዕለተ ሰንበት የሚቆመው ማኅሌት የሚዘመረው መዝሙርና የሚነበቡት ምንባቦች ሁሉ የሰውን ልጅ ለማዳን ከሰማይ ወደምድር የወረደውና ወደዚህ ዓለም የመጠው ኢየሱስ ክርስቶስ እውንተኛ የዓለም ብርሃን እንደሆነ የሚገልጡና የሚያስረዱ ናቸው፡፡

ወንጌላዊውና ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በጻፈው ወንጌል እውነተኛ ብርሃን የተባለ ማን እንደሆነ ሲገልጽ “ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበር እሱም ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምን ለምስክርነት መጣ፡፡ ስለብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ እርሱ ራሱ ብርሃን አልነበረም” በማለት ስለመጥምቁ ዮሐንስ ማንነት ከገለጠ በኋላ፡ - “ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃንስ ወደ ዓለም የመጣው ነው” በማለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ከጨለማ፤ የሰውን ልጅ ደግሞ ከጥፋት ለማዳን ወዲዚህ ዓለም የመጣ እውነተኛ ብርሃን እሱ እንደሆነ በሚገባ አረጋግጦ ጽፎት ስለሚገኝ በዚሁ “ብርሃን” እየተባለ በሚከበረው ዕለተ ሰንበት ይነበባል፤ ይተረጎማልም (ዮሐ. 1÷6-13)፡፡

ልበአምላክ የተባለ ነቢዩ ዳዊትም ዓለም በጨለማ ውስጥ በነበረበት በዚያ የኲነኔና የፍዳ ዘመን   “ፈኑ ብርሃነከ ወጽድቀከ፤ እማንቱ ይምርሃኒ ወይሰጻኒ ደብረ መቅደስከ፤ ወውስተ አብያቲከ እግዚኦ” በማለት ዘምሮአል፡፡ ትርጓሜውም “ብርሃንህንና ጽድቅህን ላክ፣ እነሱም ይምሩኝ፤ አቤቱ ወደ መቅደስህ ተራራና ወደማደሪያህ ይውሰዱኝ” ማለት ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ገና ሰው ሆኖ ከድንግል ማርያም ከመወለዱ አስቀድሞ የተነገረና እውነተኛ ብርሃን የተባለውም እሱ ራሱ ክርስቶስ እንደሆነ የሚያረጋግጥ ትንቢታዊ ቃል ነው (መዝ. 42÷3)፡፡
ነቢዩ ኢሳይያስም ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በፊት የነበረውን 5500 የፍዳና የመከራ ዘመን በጨለማ፤ ከጌችን ልደት በኋላ ያለውን ዓመተ ምሕረት ተብሎ የሚጠራውን ዘመን ደግሞ በብርሃን መስሎ በተናገረው የትንቢት ቃል “ሕዝብ ዘይብር ውስተ ጽልመት ርእየ ብርሃነ ዐቢየ፤ ወለእለ ይነብሩ ውስተ ጽልመት ወጽላሎተ ሞት ብርሃን በርሀ ሎሙ” (በጨለማ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቦች ብርሃንን አዩ፤ በሞት ጥላና በጨለማ ሀገረርም ለነበሩ ሰዎች ብርሃን ወጣላቸው) በማለት ትንቢት የተናገረውም ቦታና ጊዜ ስለሚወስነውና ጨለማ ስለሚጋርደው ከፀሐይ ወይም ከእሳትና ከመሳሰሉት ነገሮች ስለሚገኘው ብርሃን ሳይን ሕፀፅና ጉድለት ስለሌለበት ስለእውነተኛው የዓለም ብርሃን ስለኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ኢሳ. 9÷2)፡፡

የተነገረው ትንቢትና የተቆጠረው ሱባዔ ሁሉ ተፈጽሞ ዓለምን ለማዳንና የጨለማውን ዘመን አሳልፎ በዓለም ውስጥ እውነተኛ ብርሃን ለመሆን ወደዚህ ዓለም  የመጣውና ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷም ነፍስን ነሥቶ ሰው ሆኖ የተወደለው መድኃኔዓለም ክርስቶስም በመዋዕለ ትምህርቱ ስለራሱ ሲናገር “ብርሃን ወደዓለም መጥቶአልና ሰውም ሥራው ክፉ ስለሆነ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን መርጦአልና፡፡ ሥራው ክፉ የሆነ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና ክፉ ሥራው እንዳይገለጥበት ወደብርሃን አይመጣም” በማለት ሰዎች ሁሉ “እውነተኛ ብርሃን” እሱ እንደሆነ አውቀውና ተረድተው ወደእሱ እንዲመጡና በእሱም አምነው በብርሃኑ እንዲመላለሱ በምሳሌ ከማስተማሩም በላይ ወደ እውነተኛው ብርሃን የማይመጡና ጨለማውን የሚመርጡ ሁሉ መጥፎ ሥራቸው እንዳይገለጥባቸው የሚሹ ሌቦችና ወንበዴዎች ነፍሰገዳዮችም እንደሆኑ ገልጦና በሰፊው አረጋግጦ አስተምሮናል (ዮሐ. 3÷19-21)፡፡ ከዚህም ሌላ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” እያለ ይናገርና ያስተምር እንደነበር ወንጌላውያን በጻፉት ቅዱስ ወንጌል መስክረዋል፡፡

ቅዱስ ኤፍሬም የተባለው ታላቅ ሊቅም ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ባቀረበው የምስጋና ድርሰቱ “ብርሃን ዘበአማን ዘያበርህ ለኲሉ ሰብእ ለእለ ይነብሩ ውስተ ዓለም፣ በእንተ ፍቅረ ሰብእ መጻእከ ውስተ ዓለም”፤  “በዚህ ዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የምታበራ እውነተኛ ብርሃን፣ ስለሰው ፍቅር ስትል ወደ ዓለም መጣህ” በማለት ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት አድርጎ ስልጇ ስለኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን የምስጋና ቃል በዘወትር ጸሎታችን ሁል ጊዜ እየደገምነው እንገኛለን፡፡

በ4ኛው ምዕት ዓመት በደገኛው ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ዘመነ መንግሥት “ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጡር እንጂ አምላክ አይደለም” በማለት በሰው ልቡና እንክርዳድ እየዘራ የክህደት ትምህርት በማስተማር ላይ የነበረውን እርጉም አርዮስን ለማውገዝ በኒቅያ የተሰበሰቡ “ሠለስቱ ምዕት” በመባል የሚታወቁ በዕውቀት የበለፀጉ፣ ሃይማኖታቸው የፀና ምግባራቸውም የቀና 318 ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንም “…. ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር የነበረ የአብ አንድ ልጁ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን፤ እሱም ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፣ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ፣ የተፈጠረ ያይደለ የተወለደ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚስተካከል፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ ያለእርሱ ምንም የሆነ የለም …” በማለት በጸሎተ ሃይማኖት ወስነዋል ይህንንም በዘወትር ጸሎታችን በቃልም በመጽሐፍም እየደገምነው እንገኛለን፡፡

ስለዚህ ሁላችንም ቃሉን መድገም ብቻ ሳይሆን ምሥጢሩ ምን እንደሆነ በመመርመር ዓለምን ለማዳን ወደዚህ ዓለም የመጣው መድኃኔዓለም ክርስቶስ እውነተኛ የዓለም ብርሃንና እውነተኛ አምላክ መሆኑን ገልጠን በማስተማር ያላመኑትን ሁሉ ለማሳመን ብርቱ ጥረት ማድረግ ይገባናል፡፡
                                   ( ከሊቀ ብርሃናት ኢሳይያስ ወንድምአገኘሁ)

 
የሚዘራና የሚያጭድ አብረው ደስ ይላቸዋል

ጠቢቡ ሰሎሞን “ለሁሉም ጊዜ አለው” ብሎ እንደተናገረው የዘርና የመከር ወቅቶች የተለያዩ ናቸው፡፡ በግብርና ሥራ ተመድበው የሚሠሩ ገበሬዎች በዘመነ ክረምት ይዘራሉ፡፡ በዘመነ መፀው ደግሞ በክረምት የዘሩትን ሰብል ያጭዳሉ፣ ይሰበስባሉ፣ ይከምራሉ፣ ይወቃሉ፡፡ ገለባውን ከፍሬው ለይተው በጎተራ ሲያከማቹ ገለባውን በእሳት ያቃጥላሉ በዚህም ሥራቸው ራሳቸውን ችለው በልተው፣ ጠግበው ለሌላውም ይተርፋሉ፡፡
የመዝሪያ የማጨጃና የመሰብሰቢያ ጊዜያት የተለያዩ እንደመሆናቸው መጠን የሠራተኞችም የዕለት ኑሮ የተለያየ ሁኔታ አለው፡፡ በዘመነ ክረምት እየተቸገሩ እየተራቡ ያርሳሉ፣ ይዘራሉ፣ በዘመነ መፀው ደግሞ እንደልባቸው እየበሉ እየጠጡ ይሠራሉ፡፡ ይህንንም ነቢዩ ዳዊት ሲገልጽ “በለቅሶ የሚዘሩ በደስታ ያጭዳሉ፣ ይሰበስባሉ፣ ወደ እርሻቸው በሄዱ ጊዜ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ በተመለሱ ጊዜ ግን ነዶአቸውን ተሸክመው ደስ እያላቸው ይመጣሉ” ብሏል፡፡ (መዝ 125፡5-6)
በዚህ አንጻር ሊቃውንት አባቶቻችን ነቢያትን በክረምት ሐዋርያትን በበጋ ገበሬዎች መስለው ተናግረዋል፡፡ ምሳሌውንም ሲያብራሩ የክረምት ገበሬዎች ጧት ከቤታቸው ሲወጡ ምሳ አያገኙም ሞፈር ቀንበር፣ ዘርና የበሬ ዕቃዎችን በትከሻቸው ላይ አነባብረው ተሸክመው በሮቻቸውን እየነዱ ወደ እርሻቸው ይሄዳሉ፡፡ ከዚያም ከላይ ዝናቡ ከታች ጭቃው ወዠቦውና ነፋሱ ሲያንገላታቸውና ሲያዋክባቸው ይውላሉ፡፡ ማታ ወደ ቤታቸው በተመለሱም ጊዜ የረባ ምግብ አያገኙም፡፡ ጎመን ጨምቀው በልተው ያድራሉ፡፡ ክረምቱ አልፎ እህል የሚያልቅበት የወደፊት አዝመራ የማይደርስበት የቅጠል ጊዜ ነውና በቂ ምግብ ለማግኘት ያስቸግራል፡፡
የበጋ ገበሬዎች ግን ማለዳ ከቤታቸው ሲወጡ ምሳቸውን በሚገባ በልተው ይወጣሉ ቀን በሥራ በሚውሉበትም ቦታ እሸቱንና እንኩቶውን እየተመገቡ ሲሠሩ ይውላሉ፡፡ ማታ ወደ ቤታቸውም ሲመለሱ እንጀራው በሌማት ጠላው በማቶት ተዘጋጅቶ ይቆያቸዋል፡፡ ያንን እየበሉና እየጠጡ ይደሰታሉ፡፡
በክረምት ገበሬዎች የተመሰሉት ነቢያት ትንቢት በሚናገሩበትና በሚያስተምሩበት ጊዜ ከብሌት ሳይታደሱ በመንፈስ ቅዱስ ሳይጎለምሱ ልጅነትን ሳያገኙ ስለሆን መከራው ጸንቶባቸዋል፡፡ በበጋ ገበሬዎች የተመሰሉት ሐዋርያት ግን በሚያስተምሩበት ጊዜ የሚደርስባቸውን መከራ ሁሉ ከምንም አይቆጥሩትም ነበር፡፡ እንዲያውም በአደባባይ አቁመው ወቅሰው ገርፈው ስለክርስቶስ እንዳያስተምሩ አስጠንቅቀው ሲያሰናብቷቸው ደስ እያላቸው ይሄዱ ነበር፡፡ (የሐዋ ሥ. 5÷40-41)
ነቢያት ስለክርስቶስ ሰው መሆንና ከድንግል ማርያም በድንግልና ተጸንሶ በደንግልና መወለድ ወደዚህ ዓለም መጥቶ ሰው ሆኖ አሥራ ሁለቱን ሐዋርያት መምረጡን ዓለሙንም በጠቅላላ ካፍዳና ከመርገም ማዳኑን ተናግረዋል፡፡ ምሳሌን መስለዋል ሱባኤንም ቆጥረዋል፡፡ ከተናገሯቸውም ትንቢቶች ጥቂቶችን ቀጥሎ እንመልከት፡፡
ከዓበይት ነቢያት ኢሳይያስ “እነሆ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፡፡ እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች” (ትን. ኢሳ 7÷14)
“ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ፤ መካር፤ ኃያል አምላክ የዘለዓለም አባት፤ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል፡፡” (ትን. ኢሳ 9÷6) በተጨማሪም ይኸው ነቢይ “ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ ወየዓርግ ጽጌ እምጕንዱ” ከእሴይ ግንድ በትር ትወጣለች ከሥሩም ቁጥቋጦ ያፈራል፡፡” (ትን. ኢሳ 11፡1) ሲል ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት ተናግሯል፡፡ ሌሎችም ነቢያት ስለ ክርስቶስ ሰው መሆን ብዙ ምሳሌ መስለዋል ብዙ ሱባኤም ቆጥረዋል፡፡ ብዙ ትንቢትም ተናግረዋል ነገር ግን ዓረፍተ ዘመን ስለጋረዳቸው ከዘመኑ ሳይደርሱ ሲያልፉ ሐዋርያት ከዘመኑ ደርሰው ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተምረዋል፡፡ ከእርሱም ጋር አብረው በልተዋል፤ ጠጥተዋል በዓይናቸውም ተመልክተዋል፡፡
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታቸን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያትን መርጦ በሚያስተምርበት ጊዜ “እነሆ እላችኋለሁ ዓይናችሁን አንሡ አዝመራውም አሁን እንደ-ደረሰ እርሻውን ተመልከቱ የሚያጭድ ደመወዝን ይቀበላል፡፡ የሚዘራና የሚያጭድም አብረው ደስ እንዲላቸው ለዘለዓለም ሕይወት ፍሬን ይሰበስባሉ፡፡ አንዱ ይዘራል አንዱም ያጭዳል የሚለው ቃል በዚህ እውን ሆኗልና፡፡ እኔም እናንተ ያልደከማችሁትን ታጭዱ ዘንድ ሰደድኋችሁ ሌሎች ደከሙ እናንተም በድካማቸው ገባችሁ ብሏል፡፡” (የዮሐ ወን. 4÷35-38) እንዲሁም (በሉቃ. ወን. 10÷23) “እናንተ የምታዩትን የሚያዩ ዓይኖች ብፁዓን ናቸው፡፡ እላችኋለሁና እናንተ የምታዩትን ብዙዎች ነቢያትና ነገሥታት ሊያዩ ወደዱ አላዩም እናንተ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ወድደው አልሰሙም፡፡” በማለት ለደቀ መዛሙርቱ አስተምሯል፡፡
“አባት ያበጀው ለልጅ ይበጀው” እንደሚባለው ከልደተ ክርስቶስ በፊት የተነሡት አባቶች ነቢያት የተናገሩት ቃለ ትንቢት በጊዜው የነበሩትን ሐዋርያት ብቻ ሳይሆን ከእነርሱ ቀጥለው የተነሡትን የክርስቶስ ተከታዮች ሁሉ አስደስቷቸዋል፡፡ አሁንም ሆነ ወደፊት የሚነሱትና የተነሱት ትውልዶች የሚያስተምሩትና የሚማሩት ስለክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ መወለድና ስለዓለም ድኅነት የተነገሩትን ትንቢቶች የተመሰሉትን ምሳሌዎች የተቆጠሩትን ሱባኤዎች መሠረት በማድረግ ነው፡፡
ነቢያት ትንቢት የተናገሩበት ጊዜ የተለያየ ቢሆንም ትንቢቶቹ የሚታወሱበት ወቅት ዘመነ ስብከት ተብሎ ተሰይሟል፡፡ ይህም ከኅዳር 15 እስከ ታሕሳስ 29 ቀን ያለው ጊዜ ሲሆን በተለይ ከልደት በፊት ያሉት ሳምንታት ስብከት፣ ብርሃን፣ ኖላዊ እየተባሉ ይጠራሉ፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ነገር ግን የዘመኑ ፍፃሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከድንግል ማርያም የተወለደውን ልጁን ላከ” (ገላ 4÷4) ብሎ እንደገለጸው የትንቢቱ ቀጠሮ በደረሰ ጊዜ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶልናል፡፡
ገበሬ የጣረበት የጋረበት  ለብዙ ጊዜ የደከመበት የእርሻ ሰብል ደርሶለት ፍሬውን በተመገበ ጊዜ እንደሚደሰት ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ብለው ያስተማሩለት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ሐዋርያት በአካለ ሥጋ ተገኝተው ወረደ ተወለደ ብለው አስተምረው ደስ ሲላቸው ይወርዳል ይወለዳል ብለው ያስተማሩ ነቢያትም በአካለ ነፍስ ደስ ተሰኝተዋል፡፡ የሚዘራና የሚያጭድ አብረው ደስ ይላቸዋል የተባለውም ስለዚህ ነው፡፡ የሐዋርያትን አሠረ ፍኖት ተከትለን የምንማርና የምናስተምር ሁላችንም በዚህ ደስ ሊለን ይገባል፡፡
                            ወስብሐት ለእግዚአብሔር

(ከላዕከ ወንጌል በእደማርያም ይትባረክ (ቀሲስ) የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የትምህርት ሥርጭት ኃላፊ)

 
<< ጀምር < ወደኋላ 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 ወደፊት > መጨረሻ >>

ገጽ 4 ከ 111

አድራሻ

አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ

ኢ-ሜይል: aadioces@gmail.com

ድረ ገጹ ውስጥ ይፈልጉ

ሀሳበ ባሕር(የዘመን ቁጥር)

ባሕረ ሐሳብ የዘመን መቁጠሪያ

ግጻዌ