መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

መንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ርዕሰ አድባራት መንበረ ፀሐይ እንጦጦ ማርያም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ምስካየ ኅዙናን መድኃኔኃለም ገዳም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ደብረ ጽጌ ቅድስ ኡራኤል

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

መንበረ መንግሥት ቅ/ገብርኤል ገዳም

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ደብረ ኃይል ራጉኤል

የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/590538kidste_mariam.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/895720giorgis.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/903816bole_medhaniealem.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/683566trinity.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/821897entoto_mariam.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/310283meskaye_1.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/904160BEATA_MARIAM.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/578084urael.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/812647gebrie_gedam.jpg http://www.addisababa.eotc-churches.org/site/components/com_gk2_photoslide/images/thumbm/681179raguel.jpg
“ዳግም ምጽአት”

                                                                                                         ከሊቀ ብርሃናት ኢሳይያስ ወንድምአገኘሁ

ዳግም ምጽአት የሚለው ምንባበ ቃል በብዙዎች ዘንድ ግልጥና የሚታወቅ መስሎ ቢታይም ቋንቋው ግእዝ እንደመሆኑ መጠን ወደ አማርኛ መተርጎምና መብራራት ስለአለበት ወደ ሐተታውና ጥልቀት ወዳለው ምሥጢሩ ከመግባታችን በፊት ትልቁም ትንሹም የተማረውና ያልተማረውም ሁሉም በግልጥ እንዲረዳው የምሥጢሩ ቋጠሮና ውል ያለውም በዚሁ በርእሱ ላይ ስለሆነ ርእሱን ወደ አማርኛ መተርጎም አስፈላጊና ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ በዚህም መሠረት “ዳግም ምጽአት” ማለት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ወደዚህ ዓለም መምጣት ማለት ነው፡፡

በዚህ ዐቢይ ጾም ውስጥ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ያሉት ሳምንታት ሁሉም የየራሳቸው ታሪክና ሰፊ ትምህርት እንደአላቸው ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ አጭር ጽሑፍ መግለጥ የፈለግነው በጾሙ መካከል ደብረ ዘይት በመባል ስለሚታወቀው ዕለተ ሰንበትና ሳምንት ስለሆነ በውስጡም ታላቅ ምሥጢር ያለው በመሆኑ ስለእሱ በመጠኑ ማብራራት እንሞክራለን፡፡

በመሠረቱ “ደብረ ዘይት” ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለዳግም ምጽአቱ ያስተማረበትና ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታንን የገለጠበት ተራራ (ኮረብታ) ነው፡፡ “በስመ ሐዳሪ ይጼዋዕ ማኅደር”    (ቤት በባለቤቱ ስም ይጠራል) እንዲሉ ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ተራራ ስም “ደብረ ታቦር” ተብሎ የጌታችን በዓል እንደሚከበር ሁሉ ስለ ዳግም ምጽአቱና ስለምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ባስተማረበት ተራራ ስምም በዐቢይ ጾም ውስጥ አምስተኛው ሰንበት “ደብረ ዘይት” በመባል ይታወቃል፡፡ በዚሁ ዕለተ ሰንበትና ሳምንቱን ሁሉ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ስለዳግም ምጽአቱ ያስተማረው ወንጌል በሰፊው ይተነተናል ይተረካልም፡፡ በዚህ ዕለት የሚነበቡት ምንባቦችና የሚዘመሩት መዝሙራት፤ የሚቀደሰው ቅዳሴና የሚሰበከው ስብከት በአጠቃላይ የሚሰጠው ትምህርትና የሚተላለፈው መልእክት ሁሉ ዳግም ምጽአቱንና ትንሣኤ ሙታንን የተመረለከተ ነው፡፡

ወደተነሣንበት ርእስ እንመለስና “ዳግም ምጽአት” ወይም የክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት ስንል ምን ማለታችን ነው? ዳግመኛ ይመጣል በምንልበት ጊዜም የመጀመሪያው ምጽአቱ መቼ ነበር? የሚሉ ጥያቄዎች ሊነሡ ይችላሉ፡፡ መልሱም እንደሚከተለው ይሆናል፡፡ አባታችን አዳም አትብላ የተባለውን ዕፀበለስ በመብላት የእግዚአብሔርን ቃል በመጣሱና ሕግ በማፍረሱ ምክንያት ከገነት በተባረረና የሞት ሞት አደጋ በገጠመው ጊዜ እግዚአብሔር ራሱ “ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ሰው ሆኜ አድንሃለሁ” በማለት በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት በኃጢአት ምክንያት ከነበረው ክብሩ ተዋርዶ ምድረ ፋይድ ወርዶ የነበረውን የሰው ልጅ ለማዳንና ወደነበረው ክብሩ ለመመለስ ሲል ከሰማይ ወደምድር በመውረድ ወደዚህ ዓለም መጥቶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷም ነፍስን ነሥቶ ሰው ሆኖ ለመወለድ ወደዚህ ዓለም የመጣው አመጣጥ የመጀሪያው ምጽአቱ እሱ ነው፡፡ አመጣጡ ግን በብዙ ሁኔታዎች ይለያል፡፡ ይኸውም መጀመሪያ ሰው ሆኖ ዓለምን ለማዳን በመጣ ጊዜ ከቅድስት ድንግል እናቱ ነፍስና ሥጋን ተዋሕዶ ሰው በመሆኑ ምክንያት በሰዎች ሁሉ ላይ ይደርስ የነበረውን ውርደት ገንዘብ አድርጎ በበረት ተወልዶአል፤ በዚህም ዓለም 33 ዓመት ከሦስት ወር በመኖር በምድር ላይ ተመላልሶአል፡፡ በለበሰው ሥጋም ተርቦአል፣ ተጠምቶአል፣ ብዙ ፀዋትወ መከራዎችንም ተቀብሎና በመስቀል ላይ ተስቅሎ በመሞቱ የሰውን ልጅ ሞት በሞቱ ሽሮአል፡፡ ከሞት ከተነሣ በኋላም በታላቅ ክብርና ምስጋና ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡

በዳግም ምጽአቱ ግን “የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክት ሁሉ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል” ተብሎ እንደተጻፈ (ማቴ 25÷31) አመጣጡ እንደዚህ አይደለም፡፡ የዳግም ምጽአቱ አመጣጥ በታላቅ ክብርና በመለኮታዊ ግርማ በቅዱሳን መላእክት ታጅቦ በክብር ዙፋን ላይ ተቀምጦ በጻድቃንና በኃጥአን ላይ እውነተኛ ፍርድን ለመፍረድና ለሁሉም እንደ እምነቱና እንደሥራው ዋጋ ለመክፈል እንደቀድሞው በትኅትና ሳይሆን በግርማ መለኮት የሚመጣ ስለሆነ በተለይ በሕጉ ፀንተው ላልኖሩና ቃሉን ላልጠበቁ ሰዎች እጅግ አስፈሪና አስደንጋጭ ነው፡፡

የሚቀጥለው ጥያቄ ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፣ ስለ ዳግም ምጽአቱ በነገራቸው ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ “ማዕዜ ይከውን ዝንቱ ወምንትኑ ተአምሪሁ ለምጽአትከ ወለኅልፈተ ዓለም” (ማቴ. 24÷3) የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ መቼ ይሆናል? ምልክቱስ ምንድነው? ብለው ደቀ መዛሙርቱ ሐዋርያት ለብቻቸው ሆነው እንደጠየቁት ሁሉ እያንዳንዱ ሰው ዳግም ምጽአቱና የዓለም መጨረሻ መቼ ይሆን? ብሎ ሊያስብና ሊጠይቅ ይችላል፡፡ የዚህም መልስ ክርስቶስ ራሱ “ስለዚያች ቀንና ሰዓት ግን ከእግዚአብሔር ከራሱ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ማንም ማወቅ አይችልም” ሲል እንደ አስተማረው ዕለቱ፣ ጊዜውና ሰዓቱ መቼ እንደሚሆን ስለማይታወቅ “ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ” (ማቴ 24÷44) በማለት ጌታችን በነገረን ቃ መሠረት በሕገ ወንጌሉ ጸንቶ ንስሐ ገብቶና ራስን አዘጋጅቶ መኖር ብቻ ነው፡፡ ሞትም ለሰው ልጆች ዕለተ ምጽአት ስለሆነና ከሞትም በኋላ ንስሐ ስለማይኖር በዚህች ምድር ላይ በሕይወት እያለን ተዘጋጅተን መኖር ያስፈልገናል፡፡

ዳግም ምጽአቱ መጀመሪያ ዓለምን ከጥፋት ለማዳን ከመጣው አመጣጥ የሚለይበት አንዱ ምክንያትም የጊዜው ጉዳይ ነው፡፡ ወደዚህ ዓለም መጥቶ አዳምንና ዘሩን ሰው ሆኖ እንደሚያድን ለራሱ ለአዳም ቃል በገባለት ጊዜ “በሐሙስ ዕለት ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ” በማለት አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም እንደሚመጣ ዘመኑንና ጊዜውን አረጋግጦ ነግሮት ነበርና በዚሁ መሠረት ትንቢት እየተነገረለት ሱባኤም እየተቆጠረለት ቆይቶ ጊዜው ሲደርስ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል በተናገረው ቃለ ብሥራት መሠረት ወደዚህ ዓለም መጥቶ ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው ነፍስና ሥጋ ሰው ሆኖ ተወልዶአል፡፡ ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስም “ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ” በማለት የጻፈውም ይህንኑ መሠረት አድርጎ ነው (ገላ. 4÷4)፡፡

ቅዱሳን ሐዋርያት “ዳግም ምጽአቱ” መቼ እንደሚሆን ማወቅ ፈልገው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ለብቻቸው ቀርበው “ንገረን የመምጫህ ቀን መቼ ነው? ምልክቱስ ምንድነው?” በማለት በጠየቁት ጊዜ ምልክቶቹን ሲነግራቸው ጊዜውን፣ ዕለቱንና ሰዓቱን እንዳልነገራቸው ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ ጽፎት እያነበብነው እንገኛለን (ማቴ. 24÷3-51)፡፡ “ጌታችሁ በየትኛው ቀን እንደሚመጣ አታውቁምና ተዘጋጅታችሁ ኑሩ” በማለት የሰጣቸውን የማስጠንቀቂያ ቃልም ከቅዱሳት መጻሕፍት በማንበብ ሁኔታውን መረዳት እንችላለን፡፡ አመጣጡም እንደሌባ በድንገት እንደሚሆን “ነገር ግን ይህን ዕወቁ ባለቤት ሌባ የሚመጣበትን ሰዓት ቢያውቅ ኖሮ ተግቶ በጠበቀ ነበር” እያለ በምሳሌ ከማስረዳቱም በላይ “ስለዚህ እናንተም ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፤ የሰው ልጅ በምን ሰዓት እንደሚመጣ አታውቁምና” በማለት የተናገረውን ቃል ቅዱስ ማቴዎስ አሁንም እሱ ራሱ በጻፈው በዚሁ ወንጌል ዘግቦት ይገኛል (ማቴ 24÷43-44)፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስለዳግም ምጽአትና ስለዓለም መጨረሻ፤ ስለትንሣኤ ሙታንም ሁል ጊዜ የምታስተምር ቢሆንም በተለይ በዐቢይ ጾም ውስጥ “ደብረ ዘይት” በመባል በሚታወቀው ዕለተ ሰንበትና ሳምንቱን በሙሉ የበለጠ ትኩረት ሰጥታ እያስተማረች ኖራለች ወደፊትም እስከ ዕለተ ምጽአቱ ድረስ ትቀጥላለች ዕለተ ምጽአቱ (ዳግም ምጽአቱ) መቼ እንደሚሆን ዕለቱ፣ ቀኑና ሰዓቱ በግልጥ ባይታወቅም እግዚአብሔር ባቀደውና በወሰነው ጊዜ እንደሚሆንና መሆኑም እንደማይቀር፣ የታመነ ነው፡፡ ለዚህም ብዙ ማስረጃዎች አሉ፡፡ ከማስረጃዎቹም ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸውና እንመልከታቸው፡፡

1. ቅዱሳን፣ ነቢያት ስለዳግም ምጽአቱና ስለትንሣኤ ሙታን አስቀድመው የተናገሩት ትንቢት መፈጸም ስላለበትና የማይቀር መሆኑም ስለሚታመንበት ነው፡፡ ከነዚህም መካከል ልበ አምላክ የተባለው ነቢዩ ዳዊት “እግዚብሔርስ ገሐደ ይመጽእ፤ ወአምላክነሂ ኢያረምም፤ እሳት ይነድድ ቅድሚሁ” (“እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል፤ አምላክችን ዝም አይልም፤ እሳት በፊቱ ይነዳል”) በማለት የተናገረው ትንቢት በምሳሌነት ይጠቀሳል፡

2.ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ በዓለም መጨረሻ ዳግመኛ እንደሚመጣ ያስተማረው ትምህርት በቂ ማስረጃ ነው፡፡ (ማቴ 24÷30፤ 26÷64፤ ዮሐ. 14÷3)፡፡

3. ጌታችን በምድር ላይ ሊያደርግ የሚገባውን ሁሉ ፈጽሞ በመስቀል ላይ ጸዋትወ መከራዎችን ሁሉ ተቀብሎ ከሞተና ከመቃብር ከተነሣ በኋላ ወደ ሰማይ በዐረገ ጊዜ ሐዋርያት ወደሰማይ ትኩር ብለው እየተመለከቱ ሳሉ ነጭ ልብስ በለበሱ ሁለት ሰዎች የተመሰሉ መላእክት እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናተ ወደ ሰማይ የወጣው (ያረገው) ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት ሁሉ እንዲሁ ይመጣል” በማለት ስለዳግም ምጽአቱ መስክረዋል፡፡

4. ቅዱሳን ሐዋርያት በየመልእክቶቻቸው ሊቃውንትም በየመጻሕፍታቸው ስለዳግም ምጽአቱና ስለትንሣኤ ሙታን ጽፈዋል፡፡ ከእነሱም መካከል ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ሰማያት፤ የሚንዋወጡበትና የሚያልፉበት ቀድሞ የነበረው ፍጥረት ሁሉ በእሳት ነበልባል የሚቀልጥባት፤ ምድርና በእሷ ላይ ያለው ፍጥረት ሁሉ የሚቃጠልባት የእግዚአብሔር ቀን እንደሌባ በድንገት እንደምትመጣ በመግለጥ (2ኛ ጴጥ. 3÷10) ስለዓለም መጨረሻና ስለ ዳግም ምጽአት በሰፊው ያስተማረ ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስም ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ “ወንድሞች ሆይ ስለዘመናትና ስለወራት ምንም እንዲጻፍላችሁ አያስፈልጋችሁም” ካለ በኋላ “የጌታ ቀን ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ እንዲሁ ይመጣ ዘንድ ራሳችሁ አጥብቃችሁ አውቃችኋልና” በማለት በብዙ ምሳሌ መስሎ አስተምሮአል፡፡

5. ጌታችን በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ለደቀ መዛሙርቱ የነገራቸው የዳግም ምጽአቱ ምልክቶች በየጊዜው እየታዩና በድርጊትም እየተፈጸሙ በመሆናቸውና ይህም ዳግም ምጽአቱ እየተቃረበ መሆኑን በግልጥ ስለሚያመልክት ዕለተ ምጽአት እና የዓለም መጨረሻ ጊዜው መቅረቡን ያስረዳል፡፡

ለምሳሌ ሕዝብ በሕዝብ ላይ ነገሥታትም በነገሥታት ላይ እየተነሡ በመላው ዓለም ጦርነት እየተካሄደ መሆኑና የጦርነትም ወሬ በየዜና ማሠራጫው ሁሉ በአስጊ ሁኔታ እየተነገረና “ጆሮን ጭው” የሚያደርግ ወሬ ዘወትር እየተሰማ ነው፡፡ የጦርነቱም ፍጥጫና ፉክክር በቀላል መሣሪያ ሳይሆን ዓለምን በቅጽበት ማጥፋት የሚችል የኑክልየር መሣሪያ በታጠቁ ኃይሎች መካከል መሆኑ ደግሞ በእውነትም የዓለም መጨረሻ ጊዜ ቀርበአል የሚያሰኝ ነው፡፡

ቀደም ሲል በ1ኛውና በ2ኛው የዓለም ጦርነት ከዚያም ወዲህ በተለያዩ አገሮች በየጊዜው በተደረጉ ጦርነቶች ያለቀውን እና በጦርነቱ የተጎዳውን ሕዝብ ብዛት ለታሪክ ጸሐፊዎች እንተውና በአሁኑ ጊዜ አልቃኢዳ፣ አይኤስ፣ አልሸባብ … ወዘተ እየተባሉ በሚጠሩ አጥፍቶ ጠፊዎችና አሸባሪዎች እንዲሁም ስለሰው ሕይወት ደንታ በሌላቸው የሥልጣን ጥመኞችና ዘረኝነት በተጠናወታቸው ኃይሎች በሚተኮሱ ጥይቶች በየቀኑ እንደቅጠል የሚረግፈው ሕዝብና በጦርነቱ ምክንያት አካላቸውን እያጡ በከባድ ችግርና በስቃይ ውስጥ የሚገኙት ሰላማውያን ወገኖችም በዓለም ውስጥ ቁጥራቸው እየበዛ መታየቱና በአጠቃላይ የዓለም ሕዝብ ፍቅርና ሰላም አጥቶ በሽብር ውስጥ መሆኑ እነዚህና የመሳሰሉት ዘግናኝ ነገሮች ሲታዩና ሲሰሙ የዓለም መጨረሻ ጊዜ የደረሰ መሆኑን የሚያመለክቱ እውነተኛ ምልክቶች ስለሆኑ እያንዳንዱ ሰው ከኃጢአት ርቆና ንስሐ ገብቶ ወደ እግዚአብሔር በመመለስ ራሱን ከጥፋት ያድን ዘንድ ተዘጋጅቶ መኖር ይገባዋል፡፡

“ወስብሐት ለእግዚአብሔር”

 
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አምስተኛ ዓመት በዓለ ሢመት በታላቅ ድምቀት ተከበረ!!

                                                                                                                                          በዝግጅት ክፍሉ

0152

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ5ኛ ዓመት በዓለ ሢመት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መምህር ጎይቶኦም ያይኑ፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና የሥራ ኃላፊዎች ፣ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የሰንበት ት/ቤ ወጣቶች በተገኙበት ቅዳሜ የካቲት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡ 

የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ደብር ሊቃውንት “ዝንቱሰ ፓትርያርክ አባ ማትያስ ዘተፈነወ ውስተ ምድርነ ስዩም በኃበ እግዚአብሔር፡፡ ረሰዮ እግዚኡ ለውእቱ ማትያስ ይትለዓል መንበሩ፤ ስዩም በኃበ እግዚአብሔር፤ ይስአል ለክሙ በእንተ ምሕረት ነዋ ማትያስ ፓትርያርክ የሚል ያሬዳዊ መዝሙር በዝማሜ ተዘምሯል፡፡ 

ዝንቱስ ብእሲ ዘእምንእሱ ሕይወቱ ውስተ ቤተ እግዚአብሔር ከመ አብ ዘኮነ ለእጓለ ማውታ ፈጻሜ ተጽናሶን ለእቤራት እስመ ውስተ ልብሱ ክህነት ኩሉ ዓለም፡፡ ሀራሲ በእርፈ መስቀል ሰባኬ ወንጌል አባ ቅዱስ ማትያስ ክቡር ብእሴ እግዚአብሔር ለአሕዛብ መምህር ትክበር ነፍስየ በቅድሜከ ዮም ባርከኒ አባ እንሳዕ በረከተከ የሚለው ያሬዳዊ ዜማ በቁም ዜማና በወረብ በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ተዘምሯል፡፡ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን መወደስ ቅኔ ተበርክቷል፡፡ 

በመቀጠልም ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የደቡብ ማይጨው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዓሉን አስምልክተው ባስተላለፉት መልእክት ኖላዊነት ትልቁ የቤተ ክርስቲያን ሥራ ነው፡፡ ሊቀ ኖሎት ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ዋጋ ለማግኘት ተግዳሮትን ማለፍ ግድ ይላል፡፡ 

0154

“ከእናንተ ሃይማኖት የጎደለው እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤ ሕዝባችንንና ቤተ ክርስቲያናችንን ተግተን ልንጠብቅ ይገባናል፤ የምዕመናንን መንፈሳዊ ሕይወት ለመጠበቅ ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋት፣ ሰንበት ት/ቤቶችን ማቋቋም፣ ሰላምን ማስፈን፤ ዘረኝነትንና ሙስናን መቃወም፣ የቤተ ክርስቲያንን ሀብት መጠበቅ፤ የገጠሪቱ ቤተ ክርስቲያን በቂ አገልግሎት እንድታገኝ ማድረግ ይኖርብናል ፡፡ አቤቱ አምላካችን ሰላምን ስጠን እያልን ተግተን ማስተማርና መጸለይም አለብን በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ 

በመጨረሻም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚከተለውን አባታዊ መልእክት ሲያስላልፉ እግዚአብሔር አምላካችን ሁሉን የፈጠረና ያስገኘ በመሆኑ እንድንከተለው ይፈልጋል፡፡ ፈቃዱን የሚያስፈጽሙ አካላትን ሲያስቀምጥ ኑሯል፤ ወደፊትም እንደሚያስቀምጥ ገልጿል፡፡ ካህናት በመንፈሳዊ እውቀት መገንባት አለባቸው፡፡ ቅድስናን፣ ሐላፊነትን፣ ጥንቃቄን በተሞላ የሚሠራ ሥራ ዋጋ የሚያሰጥ ሲሆን ከዚህ ውጭ ከሆነ ቅጣቱ የከፋ ይሆናል፡፡ካህን ሕዝበ እግዚአብሔርን የመጠበቅ ግዴታ አለበት፡፡ ባለ አንድ፤ ባለ ሁለትና ባለ ሦስት መክሊት በተሰጣቸው መጠን ሊያተርፉ ይገባቸዋል፡፡ ምዕመናንን የሚጠብቅ ካህን ቤተ ክርስቲያን መድባ እያለች ምእመናንን ተኩላ ሲነጥቃቸው ካህናት የት አሉ? የሚያወዛውዝ ነፋስ ከየት መጣ?እግዚአብሔር ሁሉን የሰጠ ለካህኑ ነው፤ ለሕዝባችን እንዴት ሰላም መስጠት አቃተን? ቤተ ክርስቲያን ከሌለች ደግሞ እኛ መቀጠል አንችልም፡፡ ያለመታከት ማስተማርና መምከር ይጠበቅብናል፤የማይገሰስ ነፃነት፣ የማይበጠስ አንድነት አለን፤ ሕዝባችን ይህንን ሊረዳው ይገባል፤የሕዝባችን ማኅበራዊ ትስስር ጠንካራ ነው፤የራሳችንን ትተን የሌሎችን የአኗኗር ዘዴ ልንከተል አይገባንም፤ነባሩንና ተወዳጁን እሴታችንን እንዳናጣ መጠንቀቅ አለብን፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚገዛው የእግዚአብሔር ስም ነው፤ነገሮች ሁሉ ወደነበሩበት ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለስ አለባቸው፤አንዱ የሌላውን ክብር ሳይነካ ጥያቄውን ለመንግሥት ያቅርብ፤ መንግሥትም ጥያቄዎችን እየተቀበለ ይመልስ በማለት ቅዱስነታቸው አባታዊ መልእክታቸውን ካስተላለፉ በኋላ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል፡፡  

 

 
የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የሥራ ኃላፊዎች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ባለ 16 ነጥብ የአቋም መግለጫ አወጡ

810

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መ/ር ጎይቶኦም ያይኑ፤የሀገረ ስብከቱና የክፍለ ከተማ ኃላፊዎች  እንዲሁም የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች በተገኙበት፣በቅዱስነታቸው ጸሎት የተከፈተው መርሐ ግብር በቤተክርስቲያናችን ብሎም በሐገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ በመመካከር ሥራችንን እንፈትሽ፤አንድነታችንን እናጠናክር፤ቤተክርስቲያንችንን እንጠብቅና መብታችንን እናስከብር በሚል ሐሳብ የካቲት 8/2010 ዓ.ም በሀገረ ስብከቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ምክክር ተደርጓል፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩም፡- አሁን በሀገራችን ላይ እየተደረገ ያለው የሰላም ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ እንዳይመጣ የጥፋቱ አሻራም ወደ ትውልድ እንዳይተላለፍ የእኛ የአገልጋዮች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑንና ሁሉም ነገር በሥርዓትና በሕግ እንዲፈታ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

በመቀጠል መምህር ጎይቶኦም ያይኑ የሀገረ ስብከታችን ዋና ሥራ አስኪያጅ ይህ ከባድና ጽኑዕ ተጠያቂነቱ መንታ (ሰማያዊና ምድራዊ) የሆነ የኃላፊነት ቀንበር ትክሻችን ከወጣ ዘንድ እንዴት መሥራት እንዳለብን፤ ምን ላይ እንደቆምን፤ አካባቢያችን ምን እንደሚመስል መቃኘት እንድንችል፣አሠራራችንን እንድንፈትሽ፤ አንድነታችንን እንድናጠናክር፤ መብታችንን እንድናስጠብቅ፤የሥራ አፈፃፀማችን ምን መምሰል እንደሚገባው  አሠራራችንን ለመፈተሽ ቀጣይነትና ተከታታይነት ያለው የውይይት መድረክ መክፈት፣መነጋገርና መወያየት ወቅቱ የሚጠይቀው ግዴታ መሆኑን፤የገንዘብ/ የሀብት ንብረት አያያዛችን ለሕዝብ ግልጽና ተአማኒ እንዲሆን፣የካህናትና የምእመናን ግንኙነት ጠንካራና ጤናማ መደማመጥና መከባበር የነገሠበት እንዲሆን አስተዳዳሪዎቻችን በየአጥቢያው በሚገኙ በካህናት፣ በምእመናንና ወጣቶች ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት ወይም በጎ ተጽእኖ ፈጣሪነትን ለማሳደግ ብሎም የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅራዊ አሠራር ተጠብቆ እንዲቀጥል በማድረግ ረገድ የዚህ ዓይነቱ ውይይት እንደሚኖር በዚህም መሠረት ምንም እንኳን ወቅቱ የጾምና የጸሎት ቢሆንም ጸሎትን ከሥራ ሥራን ከጸሎት ጋር እያጣመርን መጓዝ ስለሚገባን ያሉብንን ጉድለቶች በማረም ጠንካራ ጎናችንን ይበልጥ በማጎልበት በሚያስችል ሁኔታ ላይ በጥልቀት እንድንወያይ በሚል የተናገሩትን መነሻ በማድረግ ጥልቅ  ውይይት ከተደረገ በኋላ ተሰብሳቢዎቹ የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡ 

1.ከቅዱስ ሲኖዶስና ከቅዱስ አባታችን በሚሰጠን አንድ ወጥ መመሪያ መሠረት ለመሥራት አንድነታችንንና ሕብረታችንን አጠናክረን ቤተ ክርስቲያንና ሕዝብን ከችግር ለመጠበቅ የጠራውን እውነተኛይቱን የኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ለሕዝባችን በጠራ መንገድ ከወትሮው የበለጠ ለማስተማር ቃል ገብተናል፣ 

2.የክርስቶስ የማዳን ትምህርት ዘርና ጎሳን ሕዝብና አሕዛብን አንድ ያደረገ ወደ አንዲት ሰማያዊ መንግሥት የሚጠራ ትምህርት መሆኑን ስለ ምንረዳ በክርስቶስ ትምህርትና ከአባቶቻችን በወረስነው ትምህርት መሠረት ዓለም የሚገለገልበት የዘር የቀለም የጎሳ የቋንቋ ልዩነት የቤተ-ክርስቲያናችን መግለጫ ባለመሆኑ ልዩነትን አስወግደን እንደ ቤተክርስቲያን ሰው በፍቅር እየሠራን ምሳሌነታችንን በተግባር ለማረጋገጥ ቃል ገብተናል፡፡ 

3.በአደረግነው ጥብቅ ውይይትና ምክረ ሐሳብ ደረጃ በተስማማነውና በተማመነው መሠረት በአሁኑ ጊዜ የዚችን ታሪካዊትና ብሔራዊት ቤተ ክርስቲያን ነፋስ የማያወዛውዘው ማዕበል ሞገድ የማያናውጠው መዋቅሯን በመፈተን ረገድ ያልተለመደና  ክርስቲያናዊ ያልሆነ ፍጹም ኢትዮጵያዊነት ጠባይና ጠረን የሌለው እንግዳ ክስተቶች አልፎ አልፎም ቢሆን ምልክታቸው እየታየ በመሆኑ ምእመን አያያዛችን እጅግ የጠበቀ እንዲሆን፣ አዳዲስ እንግዳና ያልተለመደ ባዕዳን ድርጊቶች እየተከሰቱ ነው በተለይም በቅርቡ በደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምህረት ቅድስት ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሰምራ ካቴድራል የአጥቢያ አባልነታቸው እንኳን በውል ባልታወቁ ግለሰቦች ስብስብ የተከሰተውን ችግርና አደጋ በጽኑ እንቃወማለን ለወደፊቱም ድርጊቱ በቅዱስ ሲኖዶስና በቅዱስነትዎ እንዲሁም በከተማ አስተዳደሩና በመንግሥት  በኩል ትኩረት ተሰቶ መንግሥት የቤተክርስቲያንን ህልውና በመጠበቅ ረገድ ባለበት ኃላፊነት መሠረት ችግሩ በሕግ አግባብ እንዲፈታ እንዲደረግልን እየጠየቅን ይችን ቤተክርስቲያን ከጥፋት ለማዳን በሚደረገው ርብርቦሽ ላይ ሁላችንም ከሀገረ ስብከቱና ከቅዱስነትዎ ጎን ለመቆም ቃል ገብተናል፡፡ 

4.በአንዳንድ ቦታ እየተከሰተ ያለው ሂደት የበለጠ ተግተን እንድንሠራና የማንቂያ ደወል እንደሆነ በመረዳት በቅድሚያ የእኛን አሠራር በሚገባ ፈትሸን ራሳችንንም እየፈተሸን በሥራ ሂደት የሚታዩ ክፍተቶች ካሉ እያረምን አጥፊዎችን በሕግ አግባብ ብቻ በማረም በሕገ-ወጥ አካሂድ የሚንቀሳቀሱ ክፍሎች ምንጫቸው ማን እንደሆነ ከየት እንደሆነ ማን እንደላካቸው በማጥናትና በመረዳት በሕግና በአሠራር ለመግታት ተስማምተናል፡፡ 

5.ስብከተ ወንጌል የእግዚአብሔር ሐሳብ ወደ ሰው ልጆች የሚደርስበት አመጸኛውን ትሁት ቀማኛውን መጽዋች የምናደርግበት የአገልግሎት ትልቁ ዘርፍ በመሆኑ የወንጌል አገልግሎታችንን ከወትሮው በበለጠ አጠናክረን በመቀጠል የተለየ አመለካከት ያላቸውን በእግዚአብሔር ቃል በማነጽ ከተሳሳተ መንገድ እንዲጠበቁ ለማድረግ ቃል ገብተናል፡፡ 

6.የሰንበት ት/ቤት ልጆቻችን በሃይማኖትና በመልካም ሥነ ምግባር ታንጸው የሚያድጉበት ቢሆንም በሚጠበቀው ዓላማ መሠረት እንዲሆን በአግባቡ ካልተያዘ ወጣቱ ትውልድ ለሠርጎ ገብ አስተሳሰብ ቅርብ በመሆኑ ይህን በመገንዘብ ወጣቱ ሃይማኖቱን እንደ አባቶቹ ሥልጣኔን እንደዘመኑ ይዞ ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግል ከአፍራሽ አስተሳሰብ እንዲርቅ አባቶቹን የሚያከብር የሚከተል ቤተክርስቲያኒቱን ለመረከብ ብቁ የሆነ ትውልድ የማነጽ ኃላፊነታችን ለመወጣት ቃል ገብተናል፡፡ 

7.የተቀመጥንበት የኃላፊነት ወንበር ተራ ሳይሆን የቤተክርስቲያን ወንበር በመሆኑ ይህን ወንበር የማስከበር የማስጠበቅ ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ትምህርት መሠረትነት የሠጠችንን መብትና ክብር ማስከበር አባቶቻችን አክብረውና አስከብረው እንዳስረከቡን ሁሉ እኛም አክብረንና አስከብረን ለትውልድ ለማስተላለፍ አሠራራችን እናራሳችንን ፈትሸን አጥፊን በመለየት በታማኝነትና በትጋት ለመሥራት ቃል እንገባለን፡

8.የቤተ ክርስቲያናችንን አስተዳደርና አሠራር እንከን የለሽ ለማድረግ የእርስ በርእስ አንድነት ተጎናጽፈን አጥፊ ሲገኝ ደግሞ ሀገረ ስብከቱ በጀመረው አግባብ በወቅቱ አጥፊዎችን ብቻ እጅግ በጥንቃቄ እየተለየ ሚዛናዊና ፍትሐዊ ውሳኔ እየተሰጠ በአንፃሩ የኃላፊዎችና ሠራተኞች ሹመትና ምደባ ብቃትን ጥራትን የሥራ ልምድን ፣ የሥነ-ምግባርን፣ አገልግሎትንና የሥራ አፈፃፀም ውጤትን ያገናዘበ እንደሆን አበክረን እንጠይቃለን፡፡ 

9.በአሁኑ ጊዜ እንደማንኛውም አስነዋሪ ተግባር ቤተክርስቲያንን እየፈተነ ያለው በክርስቶስ ትምህርት የሌለ አባቶቻችን ያላስተማሩን ያላስረከቡን አካባቢያዊ ጠባይና አመለካከት ከአሁኑ ካልተገታ ጥፋቱ ቀላል ስለማይሆን የክርስተናውንም ዓላማ የሚያናጋና የሚያደበዝዝ በመሆኑ ተምረናል አውቀናል ተራቀናል ካልን ከዚህ አስተሳሰብ ራሳችንን ነፃ አድርገን አርአያ ሆነን የምንመራውን ካህንና ሠራተኛም ነፃ ለማድረግ ይህንም በሥራ ለማሳየት ከልብ ተስማምተናል፡፡ 

10.በአንዳንድ አጥቢያ የሚኖሩ ግለሰቦች በቤተ ክርስቲያን ላይ እየተሰነዘረ ያለው ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ የቤተ ክርስቲያናችንን ሉዓላዊነት የሚፈትን የግለሰቦቹንም ክርስትና ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ በመሆኑ አስተሳሰቡንና ድርጊቱን አጥብቀን እንቃወመዋለን በአንጻሩ መደማመጥ መከባበር እንዲሰፍን እንደሰለጠነ ትውልድ ክብር ይግባቸውና አባቶቻችን እንዳቆዩን መመካከር መወያየት በሐሳብ የማመንና የማሳመን ኢትዮጵያዊነት ባህላችንን አጠናክረን ለመቀጠል ተግተን ነቅተን ለመሥራት ቃል ገብተናል፡፡ 

11.ዛሬ እንደተወያየነው ሁሉ ደካማ ጎናችንን አርመን ጠንከራ ጎናችንን አጠናክረን በቤተ ክርስቲያኒቱ መመሪያ ቀኖናና ሥርዓት መሠረት ሠርተንና አሠርተን ራሳችንና ቤተክርስቲያናችንን ከችግር ለማዳን ጠንክረን ለመሥራት ቃል ገብተናል፡፡ 

12.ከአባቶቻችን የተረከብነውን የመሪነት አደራና ሓላፊነት ጠብቀንና አስጠብቀን ለትውልድ ለማስተላለፍ ቃል እንገባለን፡፡

13.አሁን ባለን የስብከተ ወንጌል ትምህርት ብቻ ሕዝቡን በትምህርት መድረስ አጥጋቢ ሰለማይሆን ካህናት ከቤተ-ክርስቲያን አገልግሎት፣ ከቅዳሴ፣ ከማህሌት ባሻገር ከምእመናን ጋር ያላቸው ግንኙነት ተጠናክሮ ባላቸው ዕውቀትና ተግባቦት ምእመናንን ቤት ለቤት በሰንበቴ በማህበር እንዲያስተምሩ ለማድረግ ተስማምተናል፡፡ 

14.ግለሰባዊ አመለካከት ትተን ተቋማዊ አስተሳሰብ ተጎናጽፈን በተሰጠን ሓላፊነት መሠረት ሕግንና መመሪያን መሠረት አድርገን ለመሥራት ተስማምተናል፡፡ 

15.አንድነታችንን አጠናክረን እራሳችንን ፈትሸን አሰራራችንን አስተካክለን የቅዱስ ሲኖዶስና የቅዱስነትዎን መመሪያ በመቀበል ቤተክርስቲያናችንን ለመምራትና አገልግለን ለማስገልገል በጽኑ ቃል እንገባለን፡፡

16.በሁለተኛው የውይይት መርሐ ግብር ላይ በስፋትና በጥልቀት በመወያየት ከቅዱስነታቸውና ከቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያን እየተቀበለ ጉዳዩን የሚከታተል ኮሚቴ ለማቋቋም ተስማምተናል ፡፡

                                     የቅዱስነትዎ ቡራኬ ይድረሰን፡፡

 

 
<< ጀምር < ወደኋላ 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 ወደፊት > መጨረሻ >>

ገጽ 1 ከ 111

አድራሻ

አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ

ኢ-ሜይል: aadioces@gmail.com

ድረ ገጹ ውስጥ ይፈልጉ

ሀሳበ ባሕር(የዘመን ቁጥር)

ባሕረ ሐሳብ የዘመን መቁጠሪያ

ግጻዌ